የጦርነቱ መራዘም እና መዘዙ (ዴቭ ዳዊት )

የአማራ ህዝብ፥ እንደህዝብ ዘምቶ ይህንን ጦርነት በአሸናፊነት በአጭሩ መቋጨት ካልቻለና፥ አሁን እንደምናየው በወያኔ ፍላጎትና ዕቅድ የሚመራ፣ በአብይ አህመድ ሸፍጥ ቁማር እየተሰራ የሚደረግ ጦርነት፥ ultimately አማራን መቀመቅ ውስጥ የሚከት ይሆናል። በሱዳን የተካሄደው መፈንቅለ-መንግስት ለወያኔ የ ሜጋ-ሚሊየን jackpot የማሸነፍ ያህል ነው። በእርግጥ፥ አብደላ ሐምዶክ ወደ ቱርክ ያቀና ጊዜ ነበር፥ ሐምዶክን ለማስወገድ ስታቅማማ የነበረችው አሜሪካ፥ "ይሙት በቃ" ፍርድ የፈረደችበትና አልቡርሃንን አረንጓዴ መብራት ያሳየችው።

ከ1,200 ኪ.ሜ በላይ ሱዳንን የሚያዋስነው የአማራ "ክልል" አሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ አይቀሬ-አደጋ ገጥሞታል። ለወትሮው porous boarder የሆነው የአሶሳ ሱዳን ድንበር የቡርሃን፣ የሲሲ፣ የወያኔ፣ የጉሙዝ ታጣቂ መፈንጫና መውጫ መግቢያ ከመሆን አልፎ active war-front ሆኖ የመውጣቱ ጉዳይ የሳምንታት ዕድሜን ብቻ የሚፈልግ ነው።

አሁን እየታየ ያለው የአማራ ሁኔታ በአፍ "የህልውና ትግል" ይባል እንጂ፥ በተግባር ግን፥ የመደበኛ አዘቦት አኗኗርና አካሄድ ነው እየተስተናገደ ያለው። ከጊዜ፣ ከቀጣናዊ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችና ዓለማቀፍ አሰላለፎች ጋር የሚደረግ ትንቅንቅና እሽቅድድምን ታሳቢ ያደረገ ስራ እየተሰራ ላለመሆኑ ማሳያው ብዙ ነው።

አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት ጋር ያለውን ግንኙነት የማሻሻል ነገር በአብይ መንግስት በኩል ከማይታሰብበት ደረጃ አድርሶታል። አማራም የራሱን Cause ይዞ በራሱ መንገድ እንደአንድ power bloc ከመውጣት ይልቅ፥ ጥገኝነቱን አሜን ብሎ መቀበሉ፥ ዋጋ እያስከፈለውና ነገም ህልውናውን አደጋ ውስጥ ወደሚጥል ሁኔታ እየገፋው ይገኛል።

አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት በቱርክ ላይ የያዙት አቋም፥ ቱርክን pariah state የማድረግና፥ ቱርክ አጋር ልታደርጋቸው የምትፈልጋቸውን መንግስታት ከተቻለ በተፅዕኖ ከቱርክ sphere of influence ነፃ ማውጣት አልያም እነዚህን መንግስታት እንደ ሐምዶክ በመፈንቀል ለእነሱ ጥቅም የሚቆም መንግስትን መተካት እንጂ ቱርክን በቀጥታ መተናኮል አይፈልጉም። ኤርዶሃንም በእጁ ምን እንደያዘ ስለሚያውቅ ነው በምዕራቡ መንግስታት ላይ ሲደነፋ የሚውለው። ከድህረ-ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጀምሮ አሜሪካና አውሮፓ ቱርክን የሚፈልጉት፥ ቱርክ ከራሽያ አንፃር በያዘቻቸው ሁለት geopolitically choke points ምክንያት ነው፦ ቦስፈረስና ዳርዳኔለስ። የራሽያ ባህር ኃይል ወደ ሜዲትሬኒያን መግባት የሚችለው በእነዚህ የቱርክ ልሳነ-ባህር መሻገር ሲችል ብቻ ነው። የቱርክ የኔቶ አባልነት ብቸኛ አስፈላጊነትም ይኸው ነው። ኤርዶሃንን በመፈንቅለመንግስት ለመፈንቀል ሞክራ ያልተሳካለት አሜሪካ፥ ቱርክን የመነጠልና pariah state የማድረጉን ጉዳይ ግን ገፍታ እየሄደችበት ያለ ጉዳይ ነው። የቱርክ የአፍሪካ ቀንድ ዕጩ ከሆኑት አንደኛው ክንፍ ዛሬ ተመትቷል። በወያኔና ግብፅ ዘንድም ፌሽታው ደርቷል።

ይህንን ስንመለከት ነው፥ ለወትሮው ስንለፈልፍ እንደኖርነው ሁሉ፥ ጦርነቱ የቅድሚያ ቅድሚያ ተሰጥቶት፥ ህዝባችንን በሚሊየኖች አንቀሳቅሶ፥ ወረራውን መቀልበስ፣ ወራሪውንም ዳግም እንዳይነሳ አድርጎ ለመቅበር ክተት-በሚሊየኖች፣ ደጀንነት በሚሊየኖች፣ መሠረታዊ አገልግሎት ከሚሰጡ ተቋማት በቀር ሁሉን ዘጋግቶ በጣም ባጠረ ጊዜ ጦርነቱን በአጭር መቋጨት ያስፈልጋል የምንለው።

አሁን እየተሄደ ባለበት ሁኔታ ነገሮችን አስቀጥላለሁ ማለት ቀጣናዊውም አለማቀፋዊውም ሁኔታ በፍጥነት እየተቀያየሩና አማራን አጣብቂኝ ውስጥ እየከተቱ በመሆኑ፥ የመጨረሻው ውጤት መራራና ለትውልድ የሚተርፍ ሽንፈት ነው የሚሆነው።

ዴቭ ዳዊት።