የጦርነቱ መራዘም እና መዘዙ (ዴቭ ዳዊት )
የአማራ ህዝብ፥ እንደህዝብ ዘምቶ ይህንን ጦርነት በአሸናፊነት በአጭሩ መቋጨት ካልቻለና፥ አሁን እንደምናየው በወያኔ ፍላጎትና ዕቅድ የሚመራ፣ በአብይ አህመድ ሸፍጥ ቁማር እየተሰራ የሚደረግ ጦርነት፥ ultimately አማራን መቀመቅ ውስጥ የሚከት ይሆናል። በሱዳን የተካሄደው መፈንቅለ-መንግስት ለወያኔ የ ሜጋ-ሚሊየን jackpot የማሸነፍ ያህል ነው። በእርግጥ፥ አብደላ ሐምዶክ ወደ ቱርክ ያቀና ጊዜ ነበር፥ ሐምዶክን ለማስወገድ ስታቅማማ የነበረችው አሜሪካ፥ "ይሙት በቃ" ፍርድ የፈረደችበትና አልቡርሃንን አረንጓዴ መብራት ያሳየችው።
ከ1,200 ኪ.ሜ በላይ ሱዳንን የሚያዋስነው የአማራ "ክልል" አሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ አይቀሬ-አደጋ ገጥሞታል። ለወትሮው porous boarder የሆነው የአሶሳ ሱዳን ድንበር የቡርሃን፣ የሲሲ፣ የወያኔ፣ የጉሙዝ ታጣቂ መፈንጫና መውጫ መግቢያ ከመሆን አልፎ active war-front ሆኖ የመውጣቱ ጉዳይ የሳምንታት ዕድሜን ብቻ የሚፈልግ ነው። ለሙሉ ትንታኔው ዴቭ ዳዊት